kalimah.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

yohannes belay – tsegaw belete كلمات اغاني

Loading...

አምላክ ወደ ምድር ወደ እኔ መጣ
ከሃጥያት ቅጣት ሊያወጣ
እዳዬን በደሙ ከፈለና

የራሱ አረገኝ ዳግም እንደገና
አምላክ ወደ እኔ ወደ ምድር መጣ
ከሃጥያት ቅጣት ሊያወጣ
እዳዬን በደሙ ከፈለና
የራሱ አረገኝ ዳግም እንደገና

ለእኔ ነው መሞትህ
መሞትህ ለእኔ ነው
እኔን ልታከብር ነው
ክብርህን የጣልከው
መሞትህ ለእኔ ነው
መሞትህ ለእኔ ነው
እኔን ልታከብር ነው
ክብርህን የጣልከው

በአንዱ ሰው ምክንያት የሃጥያት ዘር ገባ
ፍርድ እና ኩነኔ ሰውን እየገዛ
ጸጋው ግን በለጠ በኢየሱስ የመጣው
ለዘላለም ህይወት ለጽድቅ የሚያበቃው
በአንዱ ሰው ምክንያት የሃጥያት ዘር ገባ
ፍርድ እና ኩነኔ ሰውን እየገዛ
ጸጋው ግን በለጠ በኢየሱስ የመጣው
ለዘላለም ህይወት ለጽድቅ የሚያበቃው
ለጽድቅ የሚያበቃው
ለጽድቅ የሚያበቃው
ለክብር የሚያበቃው
ለክብር የሚያበቃው
ለጽድቅ የሚያበቃው
ለጽድቅ የሚያበቃው
ለክብር የሚያበቃው
ለክብር የሚያበቃው

እዳዬን ከፍሎታል ኢየሱስ በደም ዋጋ
በላይ አስቀመጠኝ በሠማዩ ስፍራ
ጭንቀት ሃዘን ዋይታ ማይታሰብበት
በላይ አድርጎታል እራሱ ባለበት
እዳዬን ከፍሎታል ኢየሱስ በደም ዋጋ
በላይ አስቀመጠኝ በሠማዩ ስፍራ
ጭንቀት ሃዘን ዋይታ ማይታሰብበት
በላይ አድርጎታል እራሱ ባለበት
እራሱ ባለበት እራሱ ባለበት
እራሱ ባለበት ንጉሱ ባለበት

ያለልኬታ ዝቅ ዝቅ ብለህ በምስልህ ሰው ሆንክ
የውርደትን ሞት ስለእኔ ሞተህ እኔን አተረፍክ
ያለልኬታ ዝቅ ዝቅ ብለህ በምስልህ ሰው ሆንክ
የውርደትን ሞት ስለእኔ ሞተህ እኔን አጸደቅክ
እኛን አጸደቅከን እኛን አጸደቅከን
እኛን አከበርከን እኛን አከበርከን
እኛን አጸደቅከን እኛን አጸደቅከን
እኛን አከበርከን እኛን አከበርከን

كلمات أغنية عشوائية

اهم الاغاني لهذا الاسبوع

Loading...