kalimah.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

dawit cherent – fiteh كلمات اغاني

Loading...

ለካ በወይኒ ቤት ይኖራል ፃድቅ ሰው
ግፍ ያላረገ ሀሰት የከሰሰው
ለካ ቤተ መቅደስ ይኖራል ወንበዴ
የሰው ልጆች ፍትህ እንዲ ነው አንዳንዴ

ምን አይነት አለም ነው ፍትህ ያጏደለ
ጉቦኛ ለሆነ ፍርዱ ያጋደለ
እውነት ካልፈረደ በስተመጨረሻ
ድንጋይ አያደቅም የፍትህ መዶሻ

መሰሶ ያቆሙ ጉድፍ ያነፃሉ
ለነሱ ነፃነት ሌላ ይከሳሉ
በሀሰት አትፍረድ ቢሆንም ነገሩ
አሁንም ግን አሉ በመርዝ የሚሰክሩ

ምን አይነት አለም ነው ፍትህ ያጏደለ
ጉቦኛ ለሆነ ፍርዱ ያጋደለ
እውነት ካልፈረደ በስተመጨረሻ
ድንጋይ አያደቅም የፍትህ መዶሻ

የዘሩትን ማጨድ ስለተወሰነ
በምድር ህግጋት ስለተበየነ
ሸሽቶ አያመልጥም የህሊና እስረኛ
መፍረዱ አይቀርም እውነት ያለዳኛ

ምን አይነት አለም ነው ፍትህ ያጏደለ
ጉቦኛ ለሆነ ፍርዱ ያጋደለ
እውነት ካልፈረደ በስተመጨረሻ
ድንጋይ አያደቅም የፍትህ መዶሻ

كلمات أغنية عشوائية

اهم الاغاني لهذا الاسبوع

Loading...