kalimah.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

michael belayneh - timechi endehu (ትመጪ እንደሁ) كلمات الأغنية

Loading...

timechi endehu (ትመጪ እንደሁ) lyrics
ትመጪ እንደሁ እያልኩ ሌት ተቀን ናፋቂ
ሰርክ የማይታክተኝ አለሁሽ ጠባቂ
ፍቅር ተደግፌ ቃልኪዳን ታቅፌ
ትመጪ እንደሁ እያልኩ ክፍት ነው ደጃፌ
አትቀርም እላለሁ በመላ በጥበብ
ምን ቀን እየገፋ እድሜዬን ብታለል
ቆፈን ቢገርፈኝም ጥብቃዬ በዝቶ
እኔ ግን እዛዉ ነኝ አላጎደልኩ ከቶ

ትመጪ እንደሁ ትመጪ እንደሁ
አለው እኔ ሳላጎል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ ትመጪ እንደሁ
አለው እኔ በፍቅር አለሁኝ እንዳለሁ

በናፍቆትሽ እሣት ነድጄ ሳልከስል
ባይንሽ በጠረንሽ መልሼ እንዳገግም
ሣዜም እኖራላሁ እሱን ስደጋግም
ካለሁበት ድረስ እግርሽ እንዲረዝም
ልምጣ ያልሽ እንደሆን ቀና ነዉ ጎዳና
ልቤ ተመላልሶ ደልድሎታልና
ምኞት የማይደክመዉ ልቤ ልበ ብርቱ
ትዝታም አይደለ ተስፋ ነዉ ቅኝቱ

ትመጪ እንደሁ ትመጪ እንደሁ
አለዉ እኔ ሳላጎል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ ትመጪ እንደሁ
አለዉ እኔ በፍቅር አለሁኝ እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ ትመጪ እንደሁ
አለሁ እኔ ሳላጎል በፍቅር እንዳለሁ
ትመጪ እንደሁ ትመጪ እንደዉኘሁ
አለሁ እኔ በፍቅር አለሁኝ እንዳለሁ

كلمات أغنية عشوائية

كلمات الأغاني الشهيرة

Loading...