kalimah.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

leul hailu - atskem befrete كلمات الأغنية

Loading...

ደጃችን ፊትለፊት ሆነና
መውጫ መመለሻው ጎዳና
ቤቴ እንኳን ልቤን ባሳርፈው

ይታያል ያንቺ ያልተቆለፈው
ሳልጠራ ለምን ትመጫለሽ
መግደፌን መስነፌን ስላየሽ
በርሽን አይኔን ስላየሽው
ሳትዘጊው ገርበብ እያረግሽው
ደጃችን ፊትለፊት ሆነና
መውጫ መመለሻው ጎዳና
ቤቴ እንኳን ልቤን ባሳርፈው
ይታያል ያንቺ ያልተቆለፈው
ሳልጠራ ለምን ትመጫለሽ
መግደፌን መስነፌን ስላየሽ
በርሽን አይኔን ስላየሽው
ሳትዘጊው ገርበብ እያረግሽው

ባንቺ ስላቅ በክፋቴ
ምንም አፍ የለኝም እስኪሽር ቅጣቴ
አሁን አርፋለሁ ከፀፀቴ
ከንግዲ አታዪኝም አትስቂም በፍረቴ
በኔ የሳቀች ጥርስ ትከደናለች
ይብላኝ እንጂ ላንቺ ነፍሴስ ጨክናለች
በኔ የሳቀች ጥርስ ትከደናለች
ይብላኝ እንጂ ላንቺ ነፍሴስ ታመልጣለች

እያወኩት መሳነፌ
ልመቻች አልሞትም ላሟሙቅ እንቅልፌ
በዘራሁት ዘር ብቀጣ
ቆርጬ እድናለሁ ያጣሁትን ባጣ
በኔ የሳቀች ጥርስ ትከደናለች
ይብላኝ እንጂ ላንቺ ነፍሴስ ወስናለች

ደጃችን ፊትለፊት ሆነና
መውጫ መመለሻው ጎዳና
ቤቴ እንኳን ልቤን ባሳርፈው
ይታያል ያንቺ ያልተቆለፈው
ሳልጠራ ለምን ትመጫለሽ
መግደፌን መስነፌን ስላየሽ
በርሽን አይኔን ስላየሽው
ሳትዘጊው ገርበብ እያረግሽው
ደጃችን ፊትለፊት ሆነና
መውጫ መመለሻው ጎዳና
ቤቴ እንኳን ልቤን ባሳርፈው
ይታያል ያንቺ ያልተቆለፈው
ሳልጠራ ለምን ትመጫለሽ
መግደፌን መስነፌን ስላየሽ
በርሽን አይኔን ስላየሽው
ሳትዘጊው ገርበብ እያረግሽው

በቃ አልሞትም ሳመነታ
ላጉል ፍቅር ስቃይ ለገዳይ ትዝታ
የምን ስስት የምን መላ
ካልጨከንኩኝ አሁን ይዞ ያጋያል ኋላ

በኔ የሳቀች ጥርስ ትከደናለች
ይብላኝ እንጂ ላንቺ ነፍሴስ ወስናለች

كلمات أغنية عشوائية

كلمات الأغاني الشهيرة

Loading...