
fikir - bihon كلمات أغنية
ሰላም… ፍቅር እባላለው
ስለኔ ልንገርህ… እውነት ማንነቴን
ፍፁም ነኝ እላለው… አላምንም ስህተቴን
ሰው የሚያስበውን… አውቃለው ጠንቅቄ
ሁሉንም ታዛቢ… እራሴን ደብቄ
ያለምን ጫጫታ… ትርምስ ችግሩ ሁሉ
መቼ ይፈጠራል… እንደኔ ቢያስቡ ቢሆኑ
ይበዛል ሰው በዳይ… ቀጣፊ አታላይ ውሸታም
የራሱን ደብቆ… የሰው ፈላጊ ነው ሰው ግሩም
አይደንቀኝም ማለፍ በቃ ብዬው
ማንም የለም እንደኔ ሁሉን አየው
እለያለው ከነሱ በጣም በጣም
ሁሉ እንደኔ ቢሆን
ይኸው ተሟገቱኝ… ምኑንም ሳያቁት
ምክሬንም በከንቱ… ሳይሰሙኝ አለፉት
ቢገባቸው ኖሮ… እኔ የማስበው
ተንኮል ክፋት አላውቅ… ልቤ ሁሌም ቅን ነው
ያለምን ጫጫታ… ትርምስ ችግሩ ሁሉ
መቼ ይፈጠራል… እንደኔ ቢያስቡ ቢሆኑ
እኔ ግን የለሁም… አልገባም ከነሱ ሞቅታ
ከሩቅ ታዛቢ ነኝ… አልፋለው ችዬ በዝምታ
አይደንቀኝም ማለፍ በቃ ብዬው
ማንም የለም እንደኔ ሁሉን አየው
እለያለው ከነሱ በጣም በጣም
ሁሉ እንደኔ ቢሆን
ሁሉ ልክ ቢሆን… ማነው ወንጀለኛ
ሁሉ ጀግና ቢሆን… ማነው ፍርሀተኛ
ሁሉ ፃዲቅ ቢሆን… ማነው ሀጥያተኛ
ሁሉ ጀግና ቢሆን… ማነው ፍርሀተኛ
መቼም ሙሉ አይሆንም
የሰው ሀሳብ ከንቱ
ታምኖ አይታመን
መች አርፎ ህይወቱ
መቼም ሙሉ አይሆንም
የሰው ሀሳብ ከንቱ
ታምኖ አይታመን
መች አርፎ ህይወቱ
መቼም ሙሉ አይሆንም
የሰው ሀሳብ ከንቱ
ታምኖ አይታመን
መች አርፎ ህይወቱ
كلمات أغنية عشوائية
- whoislonny? - bleak كلمات أغنية
- swiss (de) - schlag mich كلمات أغنية
- jah khalib - порвано платье (porvano platye) كلمات أغنية
- fallujah - prison of the mind كلمات أغنية
- the wailers - soul almighty كلمات أغنية
- saint orleans - "we dont luv em" كلمات أغنية
- son house - american defense كلمات أغنية
- cem adrian - bana ne yaptın كلمات أغنية
- ray rashad - until i see you again كلمات أغنية
- merle haggard - runaway mama كلمات أغنية